የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By amele Demisew

February 11, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ኛው መደበኛ የሥራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ማምሻውንም የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ባይፖ ቴሞን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በዘቢብ ተክላይ