የሀገር ውስጥ ዜና

የሞዛምቢክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By amele Demisew

February 11, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሞዛምቢክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማኑዌላ ዶስ ሳንቶስ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 46ኛው መደበኛ የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።