አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፋር ክልል ምክር ቤት 6ኛ የስራ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት፣ 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን በሠመራ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አሲያ ከማል ፥ ምክር ቤቱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልፀዋል።
ጉባዔው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የሚቀርበውን የስራ አስፈፃሚ የ6 ወራት የስራ ክንውን ገምግሞ ህብረተሰቡን በየደረጃው ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውሳኔዎች እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጆችንና ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡