አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት 61 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል፡፡
የኢትዮ-ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ፍሬ-ሕይወት ታምሩ ÷ በኔትወርክ ማስፋፊያ፣ በአገልግሎት ጥራት፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስጀመር በሥድስት ወራት ውስጥ 61ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም የእቅዱን 97 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ በመግለጽ ÷ 130 ዓመት ያስቆጠረው ኩባንያው 80 ነጥብ 5 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡
ኩባንያው በሥድስት ወር 23 ነጥብ 74 ቢሊየን ለመንግስት ታክስ መክፈሉም የተገለጸ ሲሆን ÷ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስተዋፅኦውን እያበረከተ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በፈትያ አብደላ