Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ካይ ሀቨርትዝ ከውድድር አመቱ ውጪ ሊሆን እንደሚችል ተነገረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) ጀርመናዊው የአርሰናል አጥቂ ካይ ሀቨርትዝ በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ከውድድር አመቱ  ውጪ ሊሆን እንደሚችል ተነገረ፡፡

ልምምድ ለማድረግ ከክለቡ ጋር ወደ ዱባይ ያመራው ሀቨርትዝ በልምምድ ላይ ባጋጠመው የጡንቻ መሸማቀቅ  ጉዳት አስከውድድር አመቱ መጨረሻ ለቡድኑ አገልግሎት እንደማይሰጥ ተነግሯል፡፡

የ25 ዓመቱ አጥቂ  አርሰናል በጨዋታ ላይ በሚፈፅማቸው የጎል አጨራርስ ችግር ሳቢያ ጠንከር ያለ የደጋፊዎች ትችት ቢቀርብበትም ምርጥ ጊዜ እያሳለፈ በሚገኘው የአርሰናል ስብስብ ውስጥ ቁልፍ ተጫዋች ነበር፡፡

በጉዳት እየታመሰ በሚገኘው የአርሰናል ስብስብ ውስጥ የክንፍ ተጨዋቾቹ ቡካዮ ሳካ እና ጋበርኤል ማርቲኔሊ  እንዲሁም አጥቂው ጋብሬል ጄሱስ ባጋጠማቸው ጉዳት እስካሁን ወደ ሜዳ መመለስ አለመቻላቸውንም  ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version