ዓለምአቀፋዊ ዜና

ትራምፕ እና ፑቲን የዩክሬን እና ሩሲያን ጦርነት ለማስቆም ድርድር እንዲጀመር ተስማሙ

By yeshambel Mihert

February 12, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ ዩክሬን ያለውን ጦርነት ማስቆም የሚያስችል ድርድር በፍጥነት እንዲጀመር ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ።

ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷”ቡድኖች ተዋቅረው በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ ተስማምተናል፤ ለዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪም ደውለን ስለ ውይይቱ እናሳውቀዋለን፤ ይህም እኔ የማደርገው ነገር ነው” ብለዋል።

ክሬምሊን ፑቲን እና ትራምፕ ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል በስልክ መነጋገራቸውን እና ለመገናኘት መስማማታቸውን አስታውቋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ዶናልድ ትራምፕ እንዴት እንደሚያሳኩት ግልጽ ባይሆንም የሩሲያ ዩክሬን ጦርነትን በፍጥነት እንደሚያስቆሙ ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወቃል።