የሀገር ውስጥ ዜና

የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አዲስ አበባ ገቡ

By amele Demisew

February 13, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዋና ፀሐፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም፣ እንኳን ወደ ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እና ውቧ የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በደህና መጡ ብለዋል።