አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬኒያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
በመሰረት አወቀ እና ብሩክታዊት አፈሩ