አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ጌዲዮን ቦኮ በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።
በመሰረት አወቀ እና ብሩክታዊት አፈሩ