አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የናይጄሪያ ቀዳማዊት እመቤት ኦሉሬሚ ቲኑቡ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ቀዳማዊት እመቤቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከ38ኛው አፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በሚካሄደው የቀዳማዊት እመቤቶች ስብሰባ ላይ ለመካፈል የተለያዩ ሀገራት ቀዳማዊት እመቤቶች አዲስ አበባ በመግባት ላይ ናቸው፡፡