አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኬንያ እና ዚምባብዌ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ ከኬንያ የውጭ እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም ሚኒስትሩ ከዚምባቡዌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሞን ማሪዋራ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም ሳይካሔድ ቆይቶ የነበረውን የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን መልሶ በማንቀሳቀስ እና አዳዲስ የትብብር መስኮችን አካቶ መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡