Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የስፖርት ትጥቆች በኢትዮጵያ መመረታቸው ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው – ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፖርት ትጥቆች በኢትዮጵያ መመረታቸው ለስፖርት ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ሲሉ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ።

ሚኒስትሯ በሀዋሳ ከተማ የሚገኘውን ኦሜጋ ጋርመንት ኢንተርፕራይዝ የስፖርት ትጥቅ ማምረቻን ጎብኝተዋል።

በ2010 ዓ.ም ወደ ስራ የገባው ኢንተርፕራይዙ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ማሽኖችን በመጠቀም የተለያዩ የህትመት ወጤቶችን እና የስፖርት ትጥቆችን የሚያመርት ነው።

በ2015 ዓ.ም የስፖርት ትጥቅ ምርት ማምረት የጀመረ ሲሆን ለሲዳማ ቡና፣ ለሀዋሳ ከተማ፣ ለአርባ ምንጭ ከተማ ስፖርት ቡድኖች እንዲሁም ለክልሎች ምርቶቹን እያቀረበ ይገኛል።

ከውጭ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን የመተካት ስራ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version