የሀገር ውስጥ ዜና

በብልሹ አሰራር የተሳተፉ 23 አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነሱ

By amele Demisew

February 14, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በብልሹ አሰራር የተሳተፉ 23 አመራሮች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የ2017 ዓ/ም የግማሽ ዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት እያቀረቡ ነው ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው እንደገለጹት ÷ የስው ኃይል ስምሪት በቅጥር፣ በዝውውርና በደረጃ እድገት ከሚታዩ ብልሹ አሰራሮች ጋር በተያያዘ 3ሺህ 646 ፋይሎች ሲመረመሩ 870 ፋይሎች ህገ-ወጥ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

በዚህም ሊባክን የነበረው ከ72 ነጥብ 6ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን አንስተዋል ።

ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በብልሹ አሰራሩ የተሳተፉ 23 አመራሮች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውንም በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በ179 የክልሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷልም ነው ያሉት።

በማቴዎስ ፈለቀ