Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀሲካ አሉፖ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል፡፡

Exit mobile version