አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጂቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል አቀባበል አድርገውላቸዋል።
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል፡፡