የሀገር ውስጥ ዜና

የፍልስጤም መሪ ማህሙድ አባስ አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

February 14, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፍልስጤም መሪ ማህሙድ አባስ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ማህሙድ አባስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ “የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪዊያንና ዘርዓ-አፍሪካዊያን” በሚል መሪ ሃሳብ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል፡፡