አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ዩኤንፋኦ) ዳይሬክተር ጄነራል ኩ ዶንግዩን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ዳይሬክተር ጄነራል ኩ ዶንግዩን በድጋሚ ማግኘታቸውንና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በውይይታቸውም፥ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ዘላቂነት እና በዘርፉ ለሚያስፈልገው ጽናት ተባብሮ የመሥራትን አስፈላጊነት በማውሳት የኢትዮጵያን ቀጣይ የግብርና ሥራ ጥረቶችን ተመልክተናል ብለዋል።