የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዛምቢያው ፕሬዚዳንት ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

February 14, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዛምቢያው ፕሬዚዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበራቸው የሁለትዮሽ ውይይት የኃይል እና የአየር ትራንስፖርት ጉዳዮችን ጨምሮ ሰፋ ያለ መጠነ-ርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል።

በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ዋዜማ ላይ ሆነን በየጊዜው በመቀያየር ላይ በሚገኘው የዓለም ሥርዓት ውስጥ የአኅጉራዊ አንድነትን ጠቀሜታ አጽንዖት ሰጥተን ተወያይተናልም ብለዋል።