ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By yeshambel Mihert

February 15, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ የግሎባል ፈንድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ፒተር ሳንድስ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል፡፡

ግሎባል ፈንድ የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ በመደገፍ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏልም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዛሬው ውይይታችንም ይኽን ትብብር በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል።