የሀገር ውስጥ ዜና

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

By amele Demisew

February 15, 2025

አዲስ አበባ፣ የካተት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለ5ኛ ዙር በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 998 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ካሳ ሻወል (ዶ/ር) ለተመራቂዎች መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ፤ በቀጣይ ለሀገራቸው ሁለንተናዊ እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት ከነበረው የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ከ58 በመቶ ወደ 87 በመቶ ከፍ ማድረግ እንደተቻለም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመ ጀምሮ ከ3 ሺህ 8 መቶ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች በማስመረቅ ሀገሪቱ የተማረ የሰው ሀይል ለማፍራት የምታደርገውን ጥረት የድርሻውን እየተወጣ ነውም ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሰቲው በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የተሻለ ነገር ለማበርከት እየሰራ እንደሚገኝም ካሳ ሻወል (ዶ/ር) አንስተዋል።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል