አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ 75 ሚሊየን ህዝብ የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የአማራ ክልል የውሀ አገልግሎቶች ፅህፈት ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በደብረብርሀን ከተማ እያከናወነ ይገኛል።
በመድረኩ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ( ዶ/ር ኢ/ር)÷ በከተማና ገጠር አካባቢዎች አሁንም የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽነት ችግርን ለመቅረፍና በዘርፉ የሚስተዋልን እጥረት ለማሻሻል እንደሚሠራ ተናግረዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ 75 ሚሊየን ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ስለመሆናቸውም ጠቁመዋል፡፡
አዳዲስ የቴክኖጂ ግብአቶችን በዘርፉ ለመተግበርም ስራዎች ስለመጀመራቸው ነው ሚኒስቴሩ የገለፁት።
የአማራ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በክልሉ የከተሞች እድገትና የህዝብ ቁጥር መጨመርን ተከትሎ የሚከሰት የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረትን ለመቅረፍ እየተሰራ ስለመሆኑ ገልፀዋል።
በኤልያስ ሹምዬ