Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ17ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎችን አስመረቀ።

በዚህም ተማሪዎቹ 223 በድህረ ምረቃ እና 389 በቅድመ ምረቃ መርሐግብር የተመረቁ ሲሆን፤ 221 ያህሉ ሴቶች መሆናቸው በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልክት ባስተላለፉበት ወቅት÷ ተመራቂዎች በተመረቁበት የሙያ መስኮች ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አስገንዝበዋል።

በተለይ የህክምናና የጤና ሳይንስ ተመራቂዎች የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች በመቅረፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በመቅደስ ደረጀ

Exit mobile version