አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ሳሌም (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢኮኖሚ እና በባህል ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ላይ መክረዋል።
በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በአሕጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የጋራ ፍላጎቶች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።