የሀገር ውስጥ ዜና

ለህዝባችን ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሁልጊዜው እንተጋለን-ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

By Feven Bishaw

February 15, 2025

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህዝባችንን ጥያቄዎች ከህዝባችን ጋር ሆነን ምላሽ ለመስጠት እንደሁልጊዜው እንተጋለን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷”እውነትና ንጋት እንደሚባለው በሀሰት ፕሮፓጋንዳ እውነትን በማዛባት ህዝብን በዘላቂነት እያደናገሩ መቆየት እንደማይቻል የአማራ ክልል ምክር ቤት የሰሞኑ የውይይት ድባብ ጥሩ ማሳያ ነው” ብለዋል።

ገቢር ነበብ ማለት እንዲህ ነው፤ ትናንትን ትመረምራለህ፤ ዛሬን ትገመግማለህ፤ነገን ትተነብያለህ፤ መሬት ላይ ባለው ወሳኝ መረጃ ላይ ተመስርተህ ትክክለኛውን መንገድ መከተል የማይቀር ሀቅ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

አሁን የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የልማት እና በድምሩ የመበልፀግ ነው ያሉት አቶ ተመስገን እኛም ሰምተናል የህዝባችንን ጥያቄዎች ከህዝባችን ጋር ሆነን ምላሽ ለመስጠት እንደሁሌው እንተጋለን ብለዋል።