Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምክር ቤቱ ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ከ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጽድቋል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ስድስት ረቂቅ አዋጆችን በአባላጫ ድምጽ አጽድቋል።

በዚህም መሰረት የክልሉን የሪጅዮ ፖሊስ ከተሞች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ፣የኢንቨስትመንት አስተዳደርን ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣ የ 2017 ዓ.ም ተጨማሪ የበጀት ረቂቅ አዋጅ፣ የክልሉን ሰንደቅ ዓላማና አርማ ለመደንገግ የወጣ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

እንዲሁም ምክር ቤቱ የወላይታ ሶዶ የግብርና ኮሌጅ ለማቋቋም የወጣ አዋጅ፣ የክልሉ የመስኖ ዉሃ ተጠቃሚዎች ማህበር አዋጅ፣ የክልሉ የበጎ ፈቃደኝነት ረቂቅ ፖሊሲን መርምሮ በሙሉ ድምፅ መፅደቁ ተመላክቷል።

የ2017 ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም የገመገመው የክልሉ ምክር ቤት የኢንቨስትመንት አስተዳደር አዋጅ፣ የከተሞች ፈርጅ ለውጥ አዋጅ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ዲላ ከተሞች በሪጅዮ ፖሊስ ከተማ ደረጃ እንዲደራጁም የወጣውን አዋጅ መፅደቁ ተገልጿል።

የክልሉ መንግስት የ2017 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት 4 ቢሊየን 204 ሚሊየን 419 ሺህ ብር ሆኖ የቀረበው ረቂቅ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

በማቴዎስ ፈለቀ

Exit mobile version