አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመላው ኢትዮጵያ ታዳጊዎች ምዘና ውድድር 2ኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታዳጊዎች ልዑክ የእውቅናና ሽልማት መርሐግብር ተደረገ ።
“የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ ሀገር “በሚል መሪ ሃሳብ ከጥር 27 እስከ የካቲት 5 ቀን 2017ዓ.ምበወላይታ – ሶዶ እና አርባ ምንጭ ከተማ በ11 የውድድር ዘርፎች መከናወኑ ይታወቃል፡፡
በውድድሩ በ55 ወርቅ ፣ 50 ብር እና 34 ነሃስ በድምሩ 139 ሚዳሊያዎች በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃን ይዞ ላጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ታዳጊ ስፖርተኞች ልዑክ በከተማ አስተዳደሩ የእውቅናና የሽልማት መርሐግብር ተከናውኗል ።
በመርሐግብሩ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን÷ታዳጊዎች የነገ ሀገር ተረካቢና ተተኪ ስፖርተኞች በመሆናቸው አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በወንድማገኝ ፀጋዬ