የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

February 15, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎንለጎን ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሱሉሁ ሳሚያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው  በቀጣናዊና በአህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡