አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
በውድድር ዓመቱ ደካማ እንቅስቃሴ እያሳዩ የሚገኙት ቶተንሃሞች እና ማንቼስተር ዩናይትዶች ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ወገብ ዝቅ ብለው በ14ኛ እና በ15ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሁለቱ ቡድኖች 3 ነጥብ ይዘው ለመውጣት ይፋለማሉ።
በትናንትናው ዕለተ የተጎዱትን አማድ ዲያሎ እና ኮቢ ማይኖን ጨምሮ የዘጠኝ ተጫዋቾችን አገልግሎት የማያገኙት ቀያይ ሰይጣኖቹ ቶተንሃምን በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ይገጥማሉ።
በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት በሚደረግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከወልቭስ ጋር 11:00 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።
ከኤቨርተን ጋር ባደረገው ጨ ዋታ ነጥብ የጣለው ሊቨርፑል ከተከታዩ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት የሚያደርገውን ጨዋታ በአንፊልድ ያካሂዳል።