ስፓርት

አትሌት ድርቤ በሊዮን 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አሸነፈች

By Mikias Ayele

February 16, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ ሊዮን በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ ድል ቀንቷታል።

ድርቤ ርቀቱን በ8 ደቂቃ 39 ሰከንድ ከ49 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡

አትሌቷ  ያስመዘገበችው ሰዓት የቦታው ፈጣን ሰዓት ሆኖ መመዘገቡም ተጠቁሟል፡፡

ሌላኛዋ አትሌት የኔዋ ንብረት ደግሞ በ8 ሰከንዶች ዘግይታ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

ድርቤ ቀደም ሲል በፈረንሳይ ሌቪን በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ቀዳሚ በመሆን ማሸነፏ ይታወሳል፡፡