የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

By yeshambel Mihert

February 17, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የግምገማ መድረኩ የክልሉን የግማሽ ዓመት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ድክምትና ጥንካሬ መለየት ያስችላል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለተስተዋሉ ተግዳሮቶች ፈጣን ምላሽ በመስጠት የዜጎችን የብልጽግና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚያስችል ነው የገለጹት፡፡

በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች መሳተፋቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡