አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት የአፍሪካ ቢሮውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር ከፈተ፡፡
የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለፖሊሲ አውጭዎች ግብዓት የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን ቢሮው እንደሚያቀርብም በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡
የጥምረቱ ፕሬዚዳንት ጀፍሪ ሳክስ (ፕ/ር) እንዳሉት÷ የጥምረቱ ተቀዳሚ ዓላማ በዓለም ላይ ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና እና ማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈን ነው።
መንግሥታትን መደገፍ ዘላቂ የልማት ግቦችን ማሳካት በመሆኑ፤ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መፍትሔ በማፈላለግ ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የጥምረቱ ቢሮም አፍሪካን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡