አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የተካፈሉ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ክብር እንደሚሰማው ገልጿል፡፡
38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ተካሂዶ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡
የጉባዔውን መጠናቀቅ ተከትሎም የበርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ አማካኝነት ወደ ሀገሮቻቸው ተመልሰዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ቦካይ፣ የብሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኤቭራስቴ ንዳሺሚዬ፣ የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፎውስቲን ታውዴራ እንዲሁም የጋምቢያ ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሙሃማድ ጃሎው አየር መንገዱን ምርጫቸው በማድረግ ወደ ሀገሮቻቸው ተመልሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚሰጠውን የላቀ አገልግሎት በማጠናከር አፍሪካውያንን እርስበርስና ከተቀረው ዓለም ጋር የማገናኘት ተልዕኮውን በትጋት እንደሚወጣ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አረጋግጧል፡፡