አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፍልሰት ፖሊሲ ልማት ዓለም አቀፍ ማዕከል ሃላፊ ሞኒካ ዛኔቴ ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ፤ በፍልሰት እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚቻልባቸውን አማራጮች መፈለግ ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።
በተለይም የፍልሰት ፖሊሲ ልማት ዓለም አቀፍ ማዕከል በአዲስ አበባ ቢሮ በሚከፍትበት ሁኔታ ዙሪያ መነጋገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።