አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሩሲያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ከልዑካቸው ጋር ተወያዩ፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ዛሬ ምሽት ከሩሲያ ፌደሬሽን ፌደራል ምክር ቤት አፈጉባዔ ቫለንቲና ማትቬዬንኮ እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተገናኝተናል” ብለዋል።
ይህም የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ግንኙነቶችን ለመዳሰስ እና ለመወያየት ጥሩ እድል መፍጠሩን ገልፀዋል፡፡