የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከዓለም ባንክ የቀጣናው ዳይሬክተር ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

February 19, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከዓለም ባንክ የቀጣናው ዳይሬክተር ዳንኤል ደሉቲዝኪይ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ላይም የዓለም ባንክ ፕሮጀክቶች በአመርቂ ሁኔታ እየተተገበሩ መሆናቸውን ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከባንኩ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር በጤና ባለሙያዎች አቅም ግንባታ፣ የሀገር ውስጥ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የማህበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽነት ማስፋት እና ዲጂታይዝ ማድረግ ላይ መምከራቸውንም ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ተሞክሮዎችን ለአፍሪካ ሀገራት የምናጋራበት መንገዶች ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል፡፡