የሀገር ውስጥ ዜና

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

By amele Demisew

February 20, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በእጩነት የቀረበለትን የ8 ካቢኔ አባላት ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ፡-

1.አቶ አሊ ከድር ፡ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

2.አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ፡-የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ

3.አቶ አሰፋ ደቼ ፡- የክልሉ ቴክኒክና ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ

4.ወይዘሮ ዘቢባ መሀመድ ናስር ፡- የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

5.አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፡- የክልሉ ጤነና ቢሮ ኃላፊ

6.አቶ አብርሃም መጫ ፡- የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ

7.አቶ ዘሪሁን እሸቱ ፡- የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

8. አቶ ጌታቸው ሌሊሾ ፡-የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

በርዕሰ መስተዳድር እንደሻዉ ጣሰዉ ዶ/ር ለአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች የቀረበውን ሹመት በማስመልከት ከምክር ቤቱ አባላት ሀሳብ አስተያየት ከተሰጠ በኃላ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡