Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል በስዊዘርላንድ ናዮን ይፋ ተደርጓል።

በዚህ መሰረትም አርሰናል ከኔዘርላንድሱ ፒ ኤስ ቪ አይንድሆቨን እንዲሁም ሊቨርፑል ከፒ ኤስ ጂ ጋር ተደልድለዋል።

በተጨማሪም ባየርን ሙኒክ ከባየር ሊቨርኩሰን፣ ክለብ ብሩገ ከአስቶንቪላ፣ ቦሩሺያ ዶርትመንድ ከሊል፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ፣ ፌይኖርድ ከኢንተር ሚላን እና ቤኔፊካ ከባርሴሎና መደልደላቸውን የሊጉ መረጃ ያመላክታል፡

Exit mobile version