የሀገር ውስጥ ዜና

በአዳማ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

February 22, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዳማ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ፣ በኦሮሚያ ክልል በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት አስተባባሪ አዲሱ አረጋ፣ የምስራቅና ሸዋ እና አርሲ ዞን አስተዳዳሪዎችና የአዳማ ከተማ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዴ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም አባገዳዎች፣ ሀደሲንቄዎች እንዲሁም ከአዳማ ከተማ አስተዳደር፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞን እና ከአርሲ ዞን የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

ኮንፈረንሱ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች እና የተቀመጡ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በፈትያ አብደላ እና መሳፍት እያዩ