የሀገር ውስጥ ዜና

በሀዋሳ ህዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

February 22, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀዋሳ ከተማ ህዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በኮንፈረንሱ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በኮንፍረንሱ ማህበረሰቡ በሚያነሳቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡