አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅግጅጋ ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
በኮንፈረንሱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን፣ በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ሃላፊ መሃመድ ሻሌ (ኢ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በህዝባዊ ኮንፈረንሱ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በሰላም እና ልማት ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።
በኮንፈረንሱ ከህብረተሰብ ለሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል፡፡
በአልማዝ መኮንን