Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በዌስትሃም ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው አርሰናል 1 ለ ዐ ተሸንፏል።

የዌስትሃምን የማሸነፊያ ጎል ጃሮድ ቦውን በ45ኛ ደቂቃ ሲያስቆጥር፥ ከአርሰናል በኩል ወጣቱ ተከላካይ ሊውስ ስኬሊ በሁለተኛው አጋማሽ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

በሌሎች የ12 ሰዓት ጨዋታዎች፣ ብራይተን ሳውዛምፕተንን 4 ለ ዐ፣ቶተንሃም ሆትስፐር ኢፕስዊች ታዎንን 4 ለ1፣ ክርስታል ፓላስ ፉልሃምን 2 ለ 0 እንዲሁም ዎልቭስ ቦርንማውዝን 1 ለ ዐ አሸንፈዋል።

በሌላ በኩል ከደቂቃዎች በኋላ 2:30 ቼልሲ ከሜዳው ውጪ አስቶን ቪላን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል።

Exit mobile version