Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማንቼስተር ሲቲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኤቲሃድ ስታዲየም ይደረጋል፡፡

አርሰናል በትናንትናው እለት በዌስትሃም ዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ ሊጉን በ8 ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ሊቨርፑል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ የነጥብ ልዩነቱን ወደ 11 ከፍ ያደርጋል፡፡

ይህም የሊጉን ዋንጫ ወደ መርሲሳይዱ ክለብ ለመውሰድ ምቹ መደላድልን ይፈጥርለታል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በሪያል ማድሪድ ሽንፈትን አስተናግዶ ከውድድሩ መሰናበቱን ተከትሎ የዛሬውን ግጥሚያ በቁጭት ከማድረጉም ባሻገር በቀጣይ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ቦታ ለማስጠበቅ ይፋለማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቀደም ብሎ ቀን 11 ሰዓት ላይ ኒውካስል ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version