ስፓርት

20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በዓድዋ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

March 01, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በትግራይ ክልል ዓድዋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን 20ኛውን የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር አስጀምረዋል።

በወንዶች ምድብ ሃጎስ ገብረሕይወት፣ ገመቹ ዲዳ  እና ሌሎች ታዋቂ  አትሌቶች መሳተፋቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡

በሴቶች ደግሞ ያለምዘርፍ የኋላው፣ እጅጋየሁ ታየ እና ለምለም ሃይሉን ጨምሮ ሌሎች የአሸናፊነት ግምት የተሰጣቸው አትሌቶች መሳተፋቸው ተጠቁሟል፡፡