አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ካራማራ መርከብ የተሠራችው በፈረንጆቹ 1978 በጣሊያን ሀገር ነው፡፡
መርከቧ ከካራማራ ጦርነት ድል በኋላ ለድሉ መታሰቢያ በሚል ካራማራ የሚለውን ስያሜ ማግኘቷን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ምንም እንኳን ዛሬ አገልግሎት እየሰጠች ባይሆንም መርከቧ በጭነት ዓይነቷ የተሽከርካሪ ጫኝ እንደነበረች ይታወሳል፡፡
የምዝገባ መለያ ቁጥሯም ‘IMO:7533745’ መሆኑ ይታወቃል፡፡
መርከቧ የተሽከርካሪ ጫኝ የነበረች ቢሆንም፤ ለኢትዮጵያ ነጋዴዎች የተለያዩ ዓይነት ጭነቶችን ከአውሮፓ እና ከዓረብ ሀገራት ወደቦች በማጓጓዝ እስከ ፈረንጆቹ 2007 አገልግሎት መስጠቷ ይገለጻል፡፡
ካራማራ መርከብ በአገልግሎት ብዛት በማርጀቷ እንዲሁም በመጠንም ሆነ ቴክኖሎጂ ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ መርከቦችን ለመግዛት በማሰብ በፈረንጆቹ 2007 በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ለሚገኝ ‘Nobel Marine Services’ ለተባለ ድርጅት ተሽጣለች፡፡
በዛሬው ዕለት የካራማራ 47ኛ ዓመት የድል በዓል በአዲስ አበባ ተከብሮ ውሏል፡፡