አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ስድስት አዳዲስ የጭነት መርከቦች ልትገዛ መሆኑን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አስታውቋል።
ድርጅቱ ከስድስቱ መርከቦች ሁለቱ በተያዘው የበጀት ዓመት ተገዝተው ወደ አገልግሎት ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጿል።
ሁለቱ አልትራማክስ የደረቅ ብትን ጭነት መርከቦች እንደሆኑና 62 ሺህ ቶን የመጫን አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።
ሌላኛው ኢቲዩ ኮንቴነር ጫኝ መርከብ ደግሞ ከ3 ሺህ እስከ 4 ሺህ ኮንቴይነር የመጫን አቅም እንዳለው ተመላክቷል።
መርከቦቹ የሀገሪቱን የገቢ ወጪ ንግድ ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸውም ተጠቁሟል።
የቀሪ አራት መርከቦች ግዥ በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚፈጸምም ነው የተገለጸው።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ 10 መርከቦች ያሏት ሲሆን፣ 1ኛውና ዓባይ ፪ የተሰኘው መርከብ 63 ሺህ ቶን እንዲሁም ቀሪዎቹ ደግሞ ከ26 ሺህ እስከ 27 ሺህ ቶን የመጫን አቅም እንዳላቸውም ተጠቁሟል።
በመሳፍንት እያዩ