አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከአንጎላ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ዣዎ ሎሬንሶ የተላከላቸውን መልዕክት ተቀብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ እና አንጎላ ለአስርት ዓመታት የቆየ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።
ኢትዮጵያ ከአንጎላ ጋር በኃይል፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በኢኖቬሽን ዙሪያ ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗንም ገልጸዋል።