የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከአንጎላ ፕሬዚዳንት የተላከላቸውን መልዕክት ተቀበሉ

By Adimasu Aragawu

March 06, 2025

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከአንጎላ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ዣዎ ሎሬንሶ የተላከላቸውን መልዕክት ተቀብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ እና አንጎላ ለአስርት ዓመታት የቆየ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።

ኢትዮጵያ ከአንጎላ ጋር በኃይል፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በኢኖቬሽን ዙሪያ ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗንም ገልጸዋል።