የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግን ጎበኙ

By Adimasu Aragawu

March 07, 2025

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ እንዳለው መኮንን፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጀማል አሕመድና የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ መብራት ተሳትፈዋል።

በጉብኝታቸውም የሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡