Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማንቼስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ 9ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኖቲንግሃም ፎረስት ማንቼስተር ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

9 ሠዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ፤ የኖቲንግሃም ፎረስትን ብቸኛ ጎል ካሉም ሁድሰን ኦዶይ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የአሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን ኖቲንግሃም ፎረስት፤ ነጥቡን ወደ 51 ከፍ በማድረግ የነበረበትን ሦስተኛ ደረጃ አስጠብቋ፡፡

ማንቼስተር ሲቲም በዚህ የውድድር ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ብቻ ዘጠነኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡

Exit mobile version