አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በፖርቹጋል ሊዝበን ከተማ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፅጌ ገብረሰላማ አሸንፋለች፡፡
አትሌት ፅጌ ርቀቱን 1 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡
ኬንያዊቷ አትሌት ሩዝ ቼፕንጌቲች 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ20 ማይክሮ ሰከንድ በመግባ 2ኛ ደረጃን ስትይዘ ለስዊድን የምትሮጠው አትሌት አበባ አረጋዊ ደግሞ 3ኛ በመሆን አጠናቅቃለች፡፡